Fana: At a Speed of Life!

በቦሌ ክፍለ ከተማ የ90 ቀናት ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በቦሌ ክፍለ ከተማ ከ323 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የ90 ቀናት ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን አስመረቁ።

በዛሬው እለት ከተመረቁት ውስጥ 85 ፕሮጀክቶች በከተማ አስተዳደሩ፣ በክፍለ ከተማው፣ በግል ባለሐብቱ እና በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ መሆናቸውን የከተማው ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ የልማት ፕሮጀክቶቹ ለስራ እድል ፈጠራ፣ የኑሮ ውድነቱ የፈጠረውን የኢኮኖሚ ጫና ለማስታገስ ፣ለከተማዋ ገጽታና ለወጣቶች ስብዕና ግንባታ ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።

ለአቅመ ደካሞች የሚውሉ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ የሸገር ዳቦና የአትክልት መሸጫ ሱቆች፣ የምገባ ማዕከላት፣ የከብትና የዶሮ ርባታ ሼዶች፣ የአደባባይ ማስዋብ፣ የልጆች መጫወቻና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ጨምሮ ሌሎች በዘጠና ቀናት እቅድ የተከናወኑ ስራዎች ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.