Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ መሬት አሰጥሃለሁ በማለት ከአንድ ግለሰብ 30 ሚሊየን ብር ቅድመ ክፍያ በመጠየቅ ገንዘብ የተቀበሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ባዶ ቦታ በከተማው ካቢኔ በምደባ አስወስንልሀለሁ በማለት ከአንድ ግለሰብ 30 ሚሊየን ብር ቅድመ ክፍያ በመጠየቅ ገንዘብ የተቀበሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

እራሱን የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ አባል እንደሆነ በማስመሰል እና በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አራራት ሆቴል አካባቢ ያለውን 5 ሺህ ካሬ ሜትር ባዶ ቦታ በከተማው ካቢኔ በምደባ አስወስንልሀለሁ በማለት የማታለል ወንጀል የፈጸሙት ፍቅረስላሴ ታደሰና ግብረ አበሮቹ በቁጥጥር ስል እንደዋሉ ተገልጿል፡፡

ግለሰቡ 30 ሚሊየን ብር የግል ተበዳይን ቅድመ ክፍያ ትከፍላለህ በማለት ተበዳዩ ምንም አይነት ጥርጣሬ እንዳያድርበት ለማድረግ በተለያየ ጊዜ የተፈረመ ሰነድ በማስመሰል እንዲሁም ራሱን የከተማው መሬት ልማትና የመልካም አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ በማድረግ ሀሰተኛ ማህተሞችን በማዘጋጀት ደብዳቤዎች ላይ በመፈረምና ለግል ተበዳዩ በማሳየት የማሳመን ስራ ሲያከናውን እንደቆየ ተጠቅሷል፡፡

በጋራ ጥቅም በመመሳጠር 1ኛ ተጠርጣሪ የግል ተበዳይ ፍቅሬ በየነ የተባሉትን መሬት መግዛት እንደሚፈልግ ካረጋገጠ በኋላ በክፍለ ከተማው ወረዳ 9 አራራት ሆቴል አካባቢ ያለውን ባዶ ቦታ በከተማው ካቢኔ በምደባ አስወስንልሀለሁ በማለት 30 ሚሊየን ብር ቅድመ ክፍያ ትከፍላለህ በማለት ካቢኔዎች የፈረሙመበት ሰነድ በማስመሰል ሀሰተኛ ማህተሞችን በማዘጋጀት የተለያዩ ደብዳቤዎች ላይ በመፈረም ድርጊቱን መፈጸሙ ተመላክቷል፡፡

ደብዳቤዎቹን ለግል ተበዳዩ በማሳየት 2ኛ ተጠርጣሪ ታምራት እስጢፋኖስ ወደ ሚሰራበት ቢሮ በመሄድ ከሁለተኛ ተጠርጣሪ ጋር በማስተዋወቅ ሁለተኛ ተጠርጣሪም በሀሳቡ ሙሉ በሙሉ በመስማማት የግል ተበዳይን ጉዳዩ ቀላል እንደሆነና በቀላሉ ሊያስወስኑለት እንደሚችሉ በማሳመን የግል ተበዳይን ሰነዶችን እንዲያቀርብ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡

1ኛ ተጠርጣሪ ፍቅረስላሴ ታደሰ የግል ተበዳዩ ላይ እምነት እንዲያድርበት በማሰብ ወደ 3ኛ ተጠርጣሪ ዘውዱ ደገፋ የተባለው ግለሰብ ወደ ሚሰራበት ወደ ክፍለ ከተማው መሬት አስተዳደር ቢሮ በመውሰድና በማገናኘት፣ 3ኛ ተጠርጣሪም በተመሳሳይ በጉዳዩ በመስማማት ቦታው ድረስ ሂደው ልኬት እንዲፈፅሙ 4ኛ ተጠርጣሪ ቃልኪዳን አክሊሉ የተባሉት መሀንዲስ በመመደብ እና ልኬት እንዲወሰድ በማድረግ ጉዳዩን በቀላሉ ማስወሰን እንደሚችሉ በቀጥታ ለግል ተበዳይ በመናገር ከፍተኛ እምነት እንዲያድርባቸው አድርገዋል ነው የተባለው፡፡

1ኛ ተጠርጣሪ በስምምነታቸው መሰረት በተለያየ ቀን የ8 ስምንት ሚሊየን 250 ሺህ ብር ቼክ በመቀበል ተጠርጣሪዎች በጋራ በመሆን ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው ምክንያት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከከተማ አስታደደሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.