Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ሀዲያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂደዋል፡፡

በዚህም ሀዲያ ሆሳዕና ከወላይታ ድቻ ባደረጉት ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ተቀይሮ የገባው የአማካይ ተጫዋች መለሰ ሚሻሞ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ሀዲያ ሆሳዕና ወሳኝ ሶስት ነጥብ እንዲያገኝ አስችሎታል።

ውጤቱንም ተከትሎ በሊጉ አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ሀዲያ ሆሳዕና ነጥቡን ወደ 30 ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ ወላይታ ድቻ በ24 ነጥብ ከ10ኛ ደረጃ ወደ 11ኛ ዝቅ ብሏል።

ዛሬ ቀን ላይ በተካሄደ የ20ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርሐግብር መቻል ዳዊት ማሞ ባስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 አሸንፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.