Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ቀነኒሳ በቀለና አልማዝ አያና የሚሳተፉበት የለንደን ማራቶን የፊታችን እሑድ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላላቅ አትሌቶች የሚፋለሙበት የ2023 የለንደን ማራቶን የፊታችን እሑድ ሚያዚያ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል።

በውድድሩ በወንዶች ቀነኒሳ በቀለ የሚካፈል ሲሆን÷ ለአሸናፊነት ቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች መካከል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ቀነኒሳ በቀለ በርቀቱ 2 ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በመሮጥ ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ያለው አትሌት መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በተጨማሪም በውድድሩ ሌሎች ኢትዮጵያውን አትሌቶች የሚካፈሉ ሲሆን÷ ከእነዚህ መካከል አትሌት ታምራት ቶላ፣ ልዑል ገብረስላሴ፣ ሙስነት ገረመውና ብርሃኑ ለገሰ ይገኙበታል።

በዚህ ውድድር ከሚካፈሉ ሌሎች ሀገራት አትሌቶች መካከል እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ እንደሚገኝበት ተገልጿል፡፡።

ለአሸናፊነት ቀድምያ ግምት ከተሰጣቸው ኬንያዊያን አትሌቶች መካከል የባለፈው ዓመት የዚህ ውድድር አሸናፊው ኬንያዊው አሞስ ኪፕሩቶ አንዱ ነው።

በሴቶች በሚካሄደው ውድድር ደግሞ የባለፈው ዓመት የዚህ ውድድር አሸናፊ ያለምዘርፍ የኋላ ትካፈላለች።

የሪዮ 2016 10ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዋ አልማዝ አያናና የ1 ሺህ 500 የዓለም ክብረወስን ባለቤቷ ገንዘቤ ዲባባ በውድድሩ የሚካፈሉ አትሌቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

እንዲሁም የባለፈው ዓመት የበርሊን ማራቶን ሻምፒዮኗ ትግስት አሰፋ ለአሸናፊነት ቅድሚያ ግምት ያገኙ አትሌቶች መካከል ናቸው።
በዚህ ውድድር ኬንያዊቷ በሴቶች በርቀቱ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነችው ኬኒያዊቷ ብርጂድ ኮስጌ ጨምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በማራቶን የምትካፈለው የአትሌት ሲፋን ሀሰን ብርቱ ትንቅንቅ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.