Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ወልቂጤ ከተማ እና አዳማ ከተማ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ20ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ደስታ ዮሐንስ በ72ኛው እና ጀሚል ያዕቆብ በ77ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ አዳማ ከተማ በ27 ነጥብ ከነበረበት 10ኛ ደረጃ ወደ 8ኛ ከፍ ሲል ÷በአንጻሩ ኢትዮ ኤሌትሪክ በ10 ነጥብ በነበረበት 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት በተካሄደ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ሲዳማ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የወልቂጤ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቴዎድሮስ ታፈሰና ተመስገን በጅሮንድ ሲያስቆጥሩ÷የሲዳማ ከተማን ብቸኛ ግብ ደግሞ ፋሲል አበባየሁ አስቆጥሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.