በፕሪሚየር ሊጉቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡
በዚህም 9 ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስና ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን÷ ቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ0 አሸንፏል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግብ እስማኤል ኦሮ-አጎሮ አስቆጥሯል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ ሀዋሳ ከተማን 1ለ 0 አሸንፏል፡፡
አቤል ከበደ የማሸነፊያ ግቧን አስቆጥሯል፡፡