Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች እና ሌሎች ተግባራት ላይ መክረዋል፡፡

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የተገኙ ውጤቶች እና ተስፋዎች ዙሪያ መወያየታቸውንም አምባሳደር ተሾመ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለሰላም ስምምነቱ ትግበራ ከአሜሪካ በሚጠበቀው ድጋፍ ዙሪያ መምከራቸውን ጠቁመዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.