Fana: At a Speed of Life!

ሕገ ወጥ ታጣቂዎች በሰላም ወደ ሕብረተሠቡ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃዊ ወረዳ የሚስተዋለውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የአካባቢው ነዋሪዎች ከመከላከያ ሰራዊት እና ከክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር መክረዋል፡፡

ኮሎኔል መልካም በየነ ሰላም ወዳድ የሆነው የወረዳው ነዎሪ የሰላምን ዋጋ በአግባቡ በመገንዘብ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በቅንጅት መሥራቱን እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ኢመደበኛ የሆኑ አደረጃጀቶች የሀገር ሉዓላዊነትን እና የሕዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ስለሚያውኩ በቀጣናው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የጥፋት ኃይሎችን ሁሉም ሊታገላቸው ይገባል ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የፀጥታ ጉዳዮች ልዩ  አማካሪ መኳንንት መልካሙ÷ የአካባቢው ሰላም አስተማማኝ እንዲሆን የታጠቁ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ ትጥቃችውን እንዲፈቱ በጋራ መሥራት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

ሕገ ወጥነት ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዳይገቡ ስለሚያደርግ ከመከላከያ ሰራዊቱ እና ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በቅንጅት እንደሚሠሩ የአዊ ብሔረሰብ ዞን አስተዳዳሪ እንግዳ ዳኛው ተናግረዋል፡፡

የተገኝው ሰላም እንዳይቀለበስም በሕገ ወጥነት የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎች በሀገር ሽማግሌዎች እና በሃይማኖት አባቶች የተቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ሕብረተሠቡ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.