Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ፡፡

ለኢትዮጵያ ቡና መስፍን ታፈሰ፣ ሮቤል ተክለሚካኤል፣ አንተነህ ተፈራ እና አማኑኤል ዮሐንስ ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ብቸኛዋን የድሬዳዋ ጎል ያሲን ጀማል አስቆጥሯል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 30 በማድረስ ከሀድያ ሆሳዕና እና ፋሲል ከነማ ጋር እኩል 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

ምሽት 12፡00 ላይ ባሕርዳር ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ያደረጉት ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

የባሕር ዳር ከተማን ጎሎች ሃብታሙ ታደሰ እና አደም አባስ እንዲሁም የኢትዮጵያ መድንን ሳይመን ፒተር እና ሀቢብ ከማል አስቆጥረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.