Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የጽሑፍ ሥራዎች የሚያሳይና የሚዳስስ የመጽሃፍ ዐውደ ርዕይ በአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት ከዛሬ ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ በአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ተከፈተ።
 
በአውደ ርዕዩ ላይ በአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ቋሚ “የጠቅላይ ሚኒስትር ቤተ ንባብ” ይፋ ሆኗል።
 
“በጠቅላይ ሚኒስትር ቤተ ንባብ” ላይ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ አንስቶ ለንባብ ያበቋቸው መጻሕፍት ቀርበዋል።
 
በአብርሆት የተዘጋጀው የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ከሚያዚያ 24 እስከ ሚያዚያ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ለስድስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
 
“ቃል፤ ተግባር፤ ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የመጻሕፍት አውደ ርዕይ የንባብ ባሕልን ማጎልበትን ዓላማ ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።
 
በአውደ ርዕዩ ማስጀመሪያ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት የፕሬስ ሴክሪታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩምን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎችና ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.