Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ልማት ኤጀንሲ – ለአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ልማት ኤጀንሲ – ለአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት ዋና ጸሐፊ ናርዶስ በቀለ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በኔፓድ የልማት መርሐግብሮች አተገባበር እና የሀገራት ሚና ላይ መክረዋል፡፡

አቶ ደመቀ በውይይቱ እንደገለፁት÷ የኔፓድ የልማት መርሐ ግብሮች በአፍሪካ ድህነትን ለመቀነስ እየተደረገ ላለው ጥረት ጉልህ እገዛ አለው፡፡

ለልማት መርሐ ግብሮቹ ተፈፃሚነት ኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶም አቶ ደመቀ ለዋና ጸሐፊዋ ገለፃ አድርገዋል፡፡

ሰላምን የማፅናት እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎችን መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ኔፓድ በአህጉሪቱ የሚያከናውናቸውን የልማት ተግባራት አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ናርዶስ በቀለ በበኩላቸው÷ የኔፓድ የልማት መርሐግብሮች የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 በሚል ለያዛቸው የዕድገት ዕቅዶች መሳካት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋ ብለዋል፡፡

ኔፓድ የወጠናቸውን ዕቅዶች ተግባዊ በማድረግ ረገድ ያሉ የፋይናንስ ጉድለቶችን ለመሙላት የሃብት ማሰባሰብ ሥራ አስፈላጊ መሆኑንም ገልፀዋል።

ኔፓድ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው የልማት ትብብር በግብርና፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢተርፕራይዞች እንዲሁም መሰል በሆኑ የልማት መስኮች እንደሚቀጥል ተገልጿል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.