Fana: At a Speed of Life!

ሃላንድ የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ክብረ ወሰን ሰበረ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጫዋች ኧርሊንግ ሃላንድ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።

የ22 አመቱ ኖርዌያዊው አጥቂ ትናንት ምሽት ክለቡ ማንቼስተር ሲቲ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ባደረገው ጨዋታ በሊጉ 35ኛ ጎሉን አስቆጥሯል።

ይህም ከዚህ ቀደም በቀድሞወቹ እንግሊዛውያን አጥቂዎች አንዲ ኮል እና አለን ሽረር በአንድ የውድድር አመት የተመዘገበውን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ክብረ ወሰን እንዲሰብር አስችሎታል።

ሁለቱ አጥቂዎች በ34 ጎሎች በአንድ የውድድር አመት የተመዘገበውን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ክብረ ወሰን በጋራ ይዘውት ቆይተው ነበር።

ሃላንድ በሊጉ 5 ቀሪ ጨዋታዎች በመኖራቸው ተጨማሪ ጎሎችን ያስቆጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.