Fana: At a Speed of Life!

ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ሐዋሳ ከተማን እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልቂጤ ከተማን አሸነፉ፡፡

9፡00 ላይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሔደው ጨዋታ÷ ፍሊፕ አጃህ በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ሲዳማ ቡና ተጋጣሚውን ረትቷል፡፡

በሌላ በኩል 12፡00 ላይ ወልቂጤ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉት የ22ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በፈረሰኞቹ 2 ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ረመዳን የሱፍ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ለቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ጌታነህ ከበደ ለወልቂጤ ከተማ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ በ51 ነጥብ 1ኛ፣ ሐዋሳ ከተማ በ31 ነጥብ 8ኛ፣ ወልቂጤ ከተማ በ25 ነጥብ 12ኛ እንዲሁም ሲዳማ ቡና በ24 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

እስማኤል ኦሮ አጎሮ 21 (ከቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ጌታነህ ከበደ 15 (ከወልቂጤ ከተማ) እና ቢኒያም ጌታቸው 11 (ከድሬዳዋ ከተማ) የፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ናቸው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.