Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የኮንትራት ውል ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ49 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የኮንትራት ውል ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) (ኢ/ር) እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ አያሌው (ኢ/ር)ፈርመውታል፡፡

ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) (ኢ/ር) በስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት÷ፕሮጀክቱ በሶማሌ ክልል ሊበን ዞን ጉራዳሞሌ ወረዳ የሚተገበር ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ለድርቅ ተጋላጭ በሆነ አከባቢ የሚገነባ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት እንደመሆኑ በተቀመጠው የግንባታ ጊዜ ወቅቱን ጠብቆ በጥራት በልዩ ትኩረት እንዲከናወንም አሳስበዋል፡፡

ዮናስ አያሌው (ኢ/ር)በበኩላቸው÷ተቋማቸው የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው በመሆኑ በገቡት ውል መሠረት ፕሮጀክቱን እንደሚያጠናቀቁ ገልጸዋል።

ይህ የባለብዙ መንደር የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም የሚችል የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ከ49 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.