Fana: At a Speed of Life!

በሐረር ከተማ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረር ከተማ ‘‘ለሠላም እሮጣለሁ’’ በሚል የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ።

“ለጋራ ሠላም በጋራ እንቆማለን” በሚል መሪ ቃል በሐረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽንና በምስራቃዊ እድገት ፋና አዘጋጅነት ተካሂዷል።

በጁገል ዙሪያ በተካሄደው የሩጫ ውድድር ላይ አትሌቶችን ጨምሮ በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈውበታል።

የሩጫ ውድድሩ በዋናነት በሐረርና በድሬዳዋ ህዝብ ያለውን ሠላም ወዳድነት ወደ ሌሎች አካባቢዎችም ለማስፋት እና የሠላም እንዲሁም የአንድነት ተምሳሌት የሆኑት የከተሞቹን ህዝቦች ለማመስገን እንደሆነ የምስራቃዊ ዕድገት ፋና ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አስታውቀዋል።

በሩጫው በአትሌቶች መካከል በተካሄደ ውድድር በወንዶች አብዱልአዚዝ አባስ 1ኛ ሲወጣ ፣ ሙሉጌታ ፈጠነና ምሕረት አስፋው ፣ 2ኛ እና 3ኛ ወጥተዋል።

በሴቶች ደግሞ ሠላም ፈለቀ ፣ ትዕግስት ደጀኔና መቅደስ ወንድሙ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ወጥተዋል።

በውድድሩ ላይ ከሐረር የተገኘው ሻለቃ አትሌት አሊ አብዶሽና የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ አብዱማሊክ ኡመር ለአሸናፊዎች የተዘጋጀውን ሽልማት አበርክተዋል።

ሻለቃ አትሌት አሊ አብዶሽ ፥ ሠላም የሁሉ ነገር መሰረት ነውና ሠላማችንን አጠናክረን በመቀጠል ለሀገር እድገት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ልናበረክት ይገባል በሚል መልዕክት አስተላልፏል።

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.