Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ባህር ዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህር ዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በዛሬው እለት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በ24ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሐ ግብር ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

በዚህም ቀን 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን÷ ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግብ ሮቤል ተ/ሚካኤል 52ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

አደም አባስ የማሸነፊያ ግቧን 79ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.