Fana: At a Speed of Life!

አገልግሎቱ 667 ሺህ ጉዳዮችን በማስተናገድ 1 ነጥብ 17 ቢሊየን ብር ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት 667 ጉዳዮችን በማስተናገድ ከ1 ቢሊየን 172 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አለምሸት መሸሻ እንደገለጹት÷ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎትን አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡
ባለፉት 9 ወራትም 801 ሺህ 615 ጉዳዮችን ለማስተናገድ ታቅዶ 667 ሺህ ጉዳዮችን በማስተናገድ የእቅዱን 83 በመቶ ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል፡፡
 
በዚህም ከ1 ቢሊየን 172 ሚሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 147 ነጥብ 7 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው ያስረዱት፡፡
 
የተሽከርካሪ ሽያጭና የብድር ውል ስምምነቶች ከፍተኛ ቁጥር መያዛቸውን የገለጹት ስራ አስፈጻሚው÷ ይህም ከገቢው 88 ነጥብ 84 ድርሻ ይይዛል ብለዋል።
 
በሃሰተኛ ሰነድ የመገልገል ወንጀል ተጠርጥረው 87 ጉዳዮች ወደ ሕግ እንዲቀርቡ ተደርገው ዘጠኝ ጉዳዮች በፍ/ቤት ውሳኔ የተሰጠባቸው መሆኑንም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡
 
 
በዚህም 1 ሺህ 378 ሃሰተኛ ማስረጃዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መደረጉን ጠቁመው÷ ከተያዙት ሃሰተኛ ማስረጃዎች ውስጥ 1 ሺህ 199 ያህሉ የማንነት ማረጋገጫ መታወቂያዎች መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡
 
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.