Fana: At a Speed of Life!

ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም የዋልያዎቹ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲመሩ የቆዩት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በስምምነት ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር መለያየታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ቀጣዩን አሰልጣኝ ለመምረጥ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው ውይይትም በብሄራዊ ቡድኑ በቴክኒክ ዳይሬክተርነት እየሠሩ የሚገኙት ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት ቀጣይ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ወስኗል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ በመሥራት ላይ የሚገኙትና በወቅታዊ ውጤታማነት የተሻሉ ሆነው የተገኙት የባህር ዳር ከተማ አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ደግሞ ምክትል አሰልጣኝ ሆነው እንዲሰሩ መወሰኑ ተገልጿል፡፡

ፌዴሬሽኑ ለአሰልጣኙ እና ለክለባቸው ባህርዳር ከተማ ጥያቄ አቅርቦ ፈቃደኛ በመሆናቸው ምክትል አሰልጣኝ ሆነው  ብሄራዊ ቡድኑን እንዲመሩ ከስምምነት ላይ መደረሱ ነው የተጠቆመው።

የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሹመት ደግሞ በቅርቡ ይፋ የሚደረግ  መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.