Fana: At a Speed of Life!

የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጥሏል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ እየመራ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሀዋሳ ከተማ ነጥብ ጥሏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተደረገው የ24ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከእረፍት መልስ በቸርነት ጉግሳ ጎል መምራት ቢችልም ተባረክ ሄፋሞ በፍፁም ቅጣት ምት ጎል አስቆጥሮ ሀዋሳን አቻ ማድረግ ችሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ፈረሰኞቹ ከተከታያቸው ባህርዳር ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት የሚያሰፉበትን እድል ሲያመክኑ ሀዋሳ በአንፃሩ ነጥቡን 33 በማድረስ 6ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

የአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ቡድን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በመቻል 1 ለ 0 መሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና መቻልን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ፊሊፕ አጃህ የሲዳማ ቡና የማሸነፊያ ግብን 33ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.