Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ ከፋሲል ከነማ ጋር የተጫወተው ሲዳማ ቡና በደስታ ደሙ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በተከታታይ 3 ጨዋታዎችን ማሸነፍ የቻለው ሲዳማ ቡና ከወራጅ ቀጠና ስጋት መውጣት የቻለ ሲሆን÷ ነጥቡን 33 በማድረስ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ለድሬዳዋ ከተማ እያሱ ለገሰ እና ሱራፌል ጌታቸው ግቦችን ሲያስቆጥሩ ብቸኛዋን የወልቂጤ ከተማ ግብ ደግሞ ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡

ድሬዳዋ ማሸነፉን ተከትሎ በ33 ነጥብ ሲዳማ ቡናን በግብ ክፍያ በልጦ 9ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.