Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ- ኤሌክትሪክ ወደ ከፍተኛ ሊግ ወረደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለገጣፎ ለገዳዲን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መውረዱን ያረጋገጠ ሁለተኛ ክለብ ሆኗል።

ኢትዮ- ኤሌክትሪክ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአዲስ መልክ መደረግ ከጀመረበት 1990 አንስቶ ሁለት ጊዜ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወቃል፡፡

በ2010 ላይ ከሊጉ ከወረደ በኋላ ዘንድሮ አድጎ የነበረ ቢሆንም አምስት ጨዋታዎች እየቀሩት ለገጣፎ ለገዳዲን ተከትሎ በመጣበት ዓመት መውረዱ ተረጋግጧል።

በዛሬው መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመቻል ጋር ባደረገው ጨዋታ ሁለት አቻ ተለያይቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.