Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ከ105 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበልግ እርሻ እየለማ  ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል በበልግ ወቅት እርሻ ስራ ከ105 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እየለማ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ርዕሰ መስተዳድር  ደስታ ሌዳሞና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ በበልግ ወቅት እየለማ ያለውን ማሳ እየጎበኙ ነው።

በክልሉ በበልግ ከሚለሙ ዋና ዋና ሰብሎች ከፍተኛውን ድርሻ  በሚይዘው በበቆሎ ሰብል ከ60 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመልማት ላይ እንደሚገኝ  ነው የተገለጸው።

የበቆሎ አብቃይ የሆኑት የሀዋሳ ዙሪያ፣ ቦርቻ፣ ብላቴና ደራሮ ወረዳዎች  በአመራሮቹ  እንደሚጎበኙ ተገልጿል፡፡

በክልሉ አጠቃላይ በበልግ ወቅት እርሻ ስራ ከ105 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እየለማ እንደሚገኝና ከዚህም ከ10 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ከክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

አመራሮቹ ከጉብኝቱ በኋላ በቀጣይ የመኸር እርሻ ንቅናቄና የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ይወያያሉ መባሉን ኢዜአ ዘገቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.