Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ሐዋሳ ከተማ እና መቻል ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር የሁለተኛ ቀን ውሎ የመጀመሪያ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ እና መቻል አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ተባረክ ሄፋሞ ከእረፍት መልስ በ46ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ሐዋሳ ከተማን መሪ አድርጎ ነበር።

ይሁን እንጂ ምንተስኖት አዳነ በ97ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ መቻልን አቻ አድርጋለች።

እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የአርባ ምንጭ ከተማ ሁለት ጎሎችን አሸናፊ ፊዳ በ25 ደቂቃና በ92ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረ ሲሆን÷ ቀሪዎችን ሁለት ግቦች ደግሞ እንዳልካቸው መስፍን በ36ኛው ደቂቃና አሸናፊ ኤልያስ በ78ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.