Fana: At a Speed of Life!

ሴቶችን ስንደግፍ በኢኮኖሚው ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ በማድረግ መሆን አለበት – ሶፍያ ካሳ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴቶችን ስንደግፍ በኢኮኖሚው ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ በማድረግ መሆን አለበት ሲሉ በግብርና ሚኒስቴር የኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ሶፍያ ካሳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ባለ ሀብቶች የሚያጋጥሙዋቸው ተግዳሮቶች በሚፈቱበት ዙሪያ የሚመክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

የምክክር መድረኩ የተካሄደው ከተለያዩ ክልሎች ከመጡ በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ባለሃብቶች፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የልማት ባንክ እንዲሁም የክልል አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት ነው፡፡

ሚኒስቴር ዴዔታዋ እንደገለጹት ፥ ሴቶችን ስንደግፍ በኢኮኖሚው ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ በማድረግ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

በመሆኑም በግብርናው ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶችን በመደገፍና ውጤታማ በማድረግ በኤክስፖርት ምርት ላይ አስተዋጽዖ እንዲያበርክቱ ችግሮችን መለየትና መፍታት ያስፈልጋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በዚህም ምርትና ምርታማነታቸው እንዲጨምር ማድርግ ያስችላልም ነው ያሉት፡፡

በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ከ550 በላይ ዓይነት የግብርና ቴክኖሎጂዎች ከቀረጥ ነጻ በመሆናቸው ዕድሉን እንዲጠቀሙ ተቋሙ እንደሚሰራም ጠቅሰዋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ትዕግስት አየለ ፥ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶች የሚያነሱዋቸ በተለይ ከመሬት፣ ከብድር አቅርቦትና መሰል ችግሮችን መፍታት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ዋቄ በበኩላቸው ፥ ሴት ኢንቨስተሮችን ለመደገፍ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ከ24 ሺህ በላይ ሴቶች በብድር ተጠቃሚ ሲሆኑ ፥ ከ9 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ተመቻችቶላቸው እየሰሩ ይገኛሉም ነው ያሉት፡፡

በፀጥታ ችግር ለ3 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የጋምቤላ-ሸበል-ደንቢዶሎ መንገድ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በፀጥታ ችግር ምክንያት ለሦስት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው ከጋምቤላ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል የሚወስደው መንገድ ለማኅበረሰቡ ክፍት መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በቀጠናው በተሰጠው ግዳጅ መሠረት ግዳጁን ተወጥቶ ከጋምቤላ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል ሸበል ደንቢዶሎ የሚወስደውን መንገድ ከሥጋት ነፃ ማድረግ እና ሠላም ማስፈን መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

በመከላከያ ሠራዊት የዳሎል ማዕከላዊ እዝ 104ኛራስ ደጀን ኮር 35ኛ ዋሊያ ክፍለ-ጦር ዋና አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ደሳለኝ ሙላው ÷ በአካባቢው አስተማማኝ የሠላም ማስከበር ሥራ መሠራቱን መግለፃቸውን የጋምቤል ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

ሠራዊቱን በመደገፍ ለሠላም አስተዋፅዖ ያበረከቱ የመንግስት ኃላፊዎችንና ሕዝቡንም አመሥግነዋል፡፡

የመንግስት ኃላፊዎችና ማኅበረሰቡ በሠላም መደፍረስ ምክንያት ዳግም መንገዱ እንዳይዘጋ ግንኙነታቸውን ማጠናከር እና መረጃ መለዋወጥ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

የጋምቤላ ክልል የሠላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ዮናስ አበበ ÷ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ለአከባቢው ሠላም መስፈንና ለመንገዱ መከፈት ላደረጉት ተጋድሎ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ከአጎራባች ክልሎች ህዝቦች ጋር ያለውን ትሥሥር ለማጠናከር እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

በኦሮሚያ ክልል የአንፊሎ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ነጋሽ ቀንዓ በበኩላቸው ÷ የኦሮሚያን ክልል ከጋምቤላ ክልል ጋር የሚያገናኘው መንገድ መቋረጡ በሕዝቡ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሕይወት ላይ ቀውስ ማስከተሉን አብራርተዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በአካባቢዎቹ በሠራው ሠላም የማስከበር እና ፀጥታ የማረጋገጥ ሥራ ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.