Fana: At a Speed of Life!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መቃኞ ቤተ ክርስቲያን መረቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ-ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በአቡዳቢ የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መቃኞ ቤተ ክርስቲያንን መርቀው መንፈሳዊ አገልግሎት አስጀመሩ።

የቤተ ክርስቲያኑ መቃረቢያ ቤት ዛሬ በተመረቀበት ወቅት ቡራኬ የሰጡት ቅዱስ ፓትርያርኩ ÷ “በምትፈልጉት ጊዜ ከፍታችሁ የምትገቡበት ቤ/ክ ስላገኛችሁ ደስ ብሎናል ፤ ይህንን የሚያህል ስፋት ያለውም አይቼ አላውቅም” ብለዋል።

በዕለቱ ሀገረ ስብከቱ ለግንባታ ቦታ መረከብና ለጊዜያዊ ቤተ ክርስትያን መታነጽ አስተዋፅዖ ለነበራቸው አካላት የምሥጋና እና ዕውቅና የመስጠት ሥርዓት መከናወኑን በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.