Fana: At a Speed of Life!

ከወ/ሪት ፀጋ ጠለፋ ጋር በተያያዘ ሲፈለግ የነበረው ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከወ/ሪት ፀጋ በላቸው ጠለፋ ጋር በተያያዘ ሲፈለግ የነበረው ተጠርጣሪ የኋላመብራት ወልደማሪያም በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ተጠርጣሪ የኋላመብራትን በቅርበት ሲከታተል የነበረው የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን÷በዛሬው ዕለት ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ካሳ ጨቡ÷ግለሰቡ ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ ዛሬ በሀገረ ሰላም ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋሉን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል፡፡
ጸጋ ከተለቀቀች ጀምሮ ተጠርጣሪውን ለመያዝ ፖሊስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ሰርቷልም ብለዋል፡፡
ወይዘሪት ፀጋ ስራዋን አጠናቃ ወደ ቤቷ በማምራት ላይ እንዳለች በተጠርጣሪው ተጠልፋ ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዳ ከቀናት በኋላ መገኘቷ አይዘነጋም፡፡
የወይዘሪት ፀጋ መጠለፍ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የበርካቶች የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል።
ከፍተኛ ውግዘት እና ተቃውሞ ያስተናገደውን ይህን ድርጊት በመፈፀም የተጠረጠረው ግለሰብ ተይዞ ለፍርድ እንዲቀርብ ብዙዎች ሲጠይቁ ቆይተዋል።
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.