ግብረ ኃይሉ በመዲናዋ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍጠር የተዘጋጁ ኃይሎች እንዳሉ ደርሼባቸዋለሁ አለ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍጠር የተዘጋጁ ኃይሎች እንዳሉ ደርሼባቸዋለሁ ሲል ገልጿል፡፡
የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በመግለጫውም ፥ የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በተለያዩ ጊዜያት የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ሲያካሄድ መቆየቱን አንስቷል።
በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍጠር የተዘጋጁ ኃይሎች እንዳሉ ደርሼባቸዋለሁ ብሏል።
ይህንን ተከትሎ በከተማዋ በተከታታይ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ስለሚያካሄድ ህብረተሰቡ ይህን አውቆ ትብብር እንዲያደርግ፤ በአካባቢው ላይ ፀጉረ ልውጦችን ሲመለከት ጥቆማ እንዲሰጥና አካባቢውን እንዲጠብቅ የጋራ ግብረ ኃይሉ አሳስቧል።
ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች እንዲሁም በስልክ ቁጥር +251 111 11 01 11፣ +251 115 52 63 03፣ +251 115 52 40 77፣ +251 115 54 36 78 እና +251 115 54 36 81፣ +251 115 54 36 84፣ +251 115 54 38 04፣ +251 115 31 22 08፣ +251 115 31 22 23፣ +251 115 31 22 47፣ +251 115 31 22 20፣ +251 115 31 20 63፣ +251 115 31 20 33፣ +251 115 31 21 31፣ +251 115 31 22 21፣ +251 115 31 20 42፣ +251 115 31 20 05 ጥቆማዎችን በፍጥነት እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡
በተጨማሪም በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች መረጃውን በአካል በማድረስ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪውን አቅርቧል።
የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ በቀጣይ የሚደርስበትን ውጤት ለህዝብ እየገለፀ እንደሚሄድም አስታውቋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!