ከንቲባ አዳነች ከተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሁሉም የእምነት ተቋማት ከተውጣጡ የሃይማኖት መሪዎች እና ከሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡
ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ ማምሻውን ከሁሉም የእምነት ተቋማት የሃይማኖት መሪዎች እና ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች ጋር ገንቢ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡
“በውይይታችንም÷ ሰላምን ለማፅናት በቁርጠኝነት በትብብር መስራት እንዳለብን ተስማምተናል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
“በኃይማኖቶች መካከል ያለውን ቅርበት እና ትብብር ማጠናከር ሰላምን ከማፅናት ባለፈ ለጀመርነዉ ልማትም አስፈላጊ በመሆኑ ይህንኑ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናልም” ነው ያሉት፡፡