Fana: At a Speed of Life!

ማንቸስተር ሲቲ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ አነሳ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቸስተር ሲቲ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ አንስቷል
የእንግሊዙ ማንቸስተር ሲቲ እና የጣሊያኑ ኢንተርሚላን ምሽት 4 ሰዓት ላይ በቱርኩ አታቱርክ ኦሎምፒክ ስታዲየም የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡

የፔፕ ጋርዲዮላው ማንቸስተር ሲቲ ኢንተርሚላን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ አንስቷል፡፡

በዚህም ማንቸስተር ሲቲ ሶስት ዋንጫዎች በማንሳት የውድድር ዓመቱን በስኬት አጠናቅቋል፡፡

የፍጻሜ ጨዋታውን የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻንን ጨምሮ በርካት የዓለማችን እግር ኳስ ወዳጆች በቀጥታ ተከታትለውታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.