ለ34 የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ሰኔ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ የአፍሪካ ዞን የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ከቻድ ጋር ለተደለደለው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 34 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ፡፡
ቡድኑ ለጨዋታው ለሚያደርገው ዝግጅት የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለተጫዋቾቹ ጥሪ አድርገዋል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም ሰኔ 13 ቀን 2015ዓ.ም ከ11 ሰዓት ጀምሮ በጁፒተር ሆቴል ሪፖርት በማድረግ እንዲሰበሰቡ ጥሪ መቅረቡን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡