Fana: At a Speed of Life!

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በቀጣዩ ዓመት ፋሲል ከነማን ለማሰልጠን ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

በ2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሳተፍ የጀመረው ፋሲል ከነማ የሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የቻለ ሲሆን÷ በ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ክለቡ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ደካማ አቋም ያሳየ ሲሆን÷ በ38 ነጥቦች 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

 

ወደ ቀድሞ አቋማቸው ለመመለስ ሁነኛ አሰልጣኝ ሲያፈላልጉ የቆዩት አፄዎቹ ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር አብሮለመስራት ከስምምነት መድረሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

የስምምነቱ አጠቃላይ ዝርዝር ሁኔታዎች እና ይፋዊ የፊርማ ሥነ-ስርዓትም በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቀደም ሲል በፋሲል ከነማ ውጤታማ ጊዜ ማሳለፋቸው የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.