Fana: At a Speed of Life!

በሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የማራቶን ውድድር አትሌት ብርሃኑ ነበበው እና ጠጅቱ ስዩም አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ ማራቶን ውድድር አትሌት ብርሃኑ ነበበው እና አትሌት ጠጅቱ ስዩም አሸነፉ።

39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የማራቶን ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ ተብሎ የሚጠራው ቦታ መነሻና መድረሻው አድርጎ ተካሂዷል፡፡

በማራቶን ውድድሩ በወንዶች አትሌት ብርሃኑ ነበበው ከፌደራል ፖሊስ በቀዳሚነት በመግባት ማሸነፉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እንዲሁም አትሌት ልመንህ ጌታቸው ከመቻል ሁለተኛ አትሌት ገልገሎ ጠና ከፌደራል ማረሚያ ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል።

በሴቶች የተደረገውን ውድድር ደግሞ አትሌት ጠጅቱ ስዩም ከመቻል በቀዳሚነት አጠናቃለች፡፡

እንዲሁም አትሌት አስናቀች ግርማ ከኦሮሚያ ፖሊስ ሁለተኛ ስትወጣ÷ አትሌት ብዙአገር አደራ ከንግድ ባንክ ሶስተኛ ሆነው ጨርሰዋል ።

በዚህ ውድድር 12 ክለቦች፣ ሁለት ክልሎችና አንድ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 262 ወንድና 92 ሴት አትሌቶች በድምሩ 354 አትሌት ተሳትፈዋል ።

ይህ የማራቶን ውድድር የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ የኦሊምፒክ ድል ፈር ቀዳጅና የምንጊዜም ኩራት የሆነው ሻምበል አትሌት አበበ ቢቂላን ለመዘከር ታስቦ በ1974 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄድ ውድድር ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.