Fana: At a Speed of Life!

ኮሚቴው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ትናንት ባደረገው ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡

በ28ኛ ሣምንት ፕሪሚየር ሊግ የተደረጉ ግጥሚያዎችን ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ ነው ኮሚቴው ውሳኔ ያሳለፈው፡፡

በውሳኔው መሠረትም ሰኔ 22 ቀን 2015 ዓ.ም የሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች በእኩል ሰዓት በተለያየ ሜዳ ይደረጋሉ፡፡

በመሆኑም÷ አርባምንጭ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከወልቂጤ ከተማ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ስታድየም ከቀኑ 9:00 ሰዓት የሚጫወቱ ይሆናል።

በሌላ በኩል የባሕር ዳር ከተማ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ክለቡ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ28ኛ ሣምንት ጨዋታ በ63ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያሰጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከሜዳ በመወገዱ 1 ጨዋታ እንዲታገድ ተወስኗል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.