Fana: At a Speed of Life!

አርሰናል እንግሊዛዊውን አማካይ ዲክላን ራይስን ለማስፈረም ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሰናል እንግሊዛዊውን አማካይ ዴክላን ራይስን ከዌስትሃም ዩናይትድ የክለቡ ሪከርድ በሆነ የዝውውር ዋጋ ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡

መድፈኞቹ ለ24 ዓመቱ ተጫዋች ዝውውር 100 ሚሊየን ፓውንድ ክፍያ እንዲሁም ተጨማሪ 5 ሚሊየን ፓውንድ ለፊርማ ወጪ ያደርጋሉ፡፡

አርሰናል ለተጫዋቹ ዝውውር ያቀረበውን 100 ሚሊየን ፓውንድ ክፍያ በ18 ወራት ውስጥ ለዌስትሃም ዩናይትድ የሚከፈል ይሆናል።

አርሰናል 100 ሚሊየን ፓውንድ የሚያወጣበት ዲክላን ራይስ የክለቡ የምን ጊዜም ውዱ ተጫዋች ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መድፈኞቹ ከዚህ ቀደም ኒኮላስ ፔፔን ከሊል በ72 ሚሊየን ፓውንድ ያስፈረሙበት የዝውውር ዋጋ የክለቡ ክብረ ወሰን ነበር።

አርሰናል በክረምቱ የዝውውር መስኮት አስቀድሞ ካይ ሃቨርትዝን ማስፈረሙ የሚታወስ ነው ።

በተመሳሳይ የሌስተርሲቲው አጥቂ ጄምስ ማዲሰን ወደ ቶተንሃም እንዲሁም የቼልሲው በረኛ ኤድዋርድ ሜንድ ወደ አል አህሊ በሳምንቱ የተጠናቀቁ ዝውውሮች ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.