Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል፡፡

ድሬዳዋ ከተማ እና አርባ ምንጭ ከተማ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የድሬዳዋ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አጥቂው ቢኒያም ጌታቸው በ72ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ በ39 ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 8ኛ ከፍ ሲል÷አርባ ምንጭ ከተማ ደግሞ ከነበረበት 13ኛ ደረጃ ወደ 14ኛ ዝቅ በማለት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ገብቷል።

በሌላ በኩል በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ወላይታ ድቻ እና ወልቂጤ ከተማ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

በዚህም ወላይታ ድቻ በ37 ነጥብ በነበረበት 11ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷ ወልቂጤ ከተማ በ34 ነጥብ ከነበረበት 14ኛ ደረጃ ወደ 13 ከፍ በማለት ከወራጅ ቀጠና መውጣት ችሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.