Fana: At a Speed of Life!

ባሕር ዳር ከተማ በአፍሪካ መድረክ ተሳታፊ መሆኑን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሕር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድን ነጥብ መጣሉን ተክትሎ በአፍሪካ መድረክ ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ዛሬ በተከናወነው የ29ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ0 አሸንፏል፡፡

ደስታ ዮሐንስ በመጀመሪያው አጋማሽ እንዲሁም ቢንያም አይተን እና አብዱል ከሪም ሞሐመድ (በራሱ መረብ ላይ) ጎሎቹን አስቆጥዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ባሕር ዳር ከተማ 2 ጨዋታዎች እየቀሩት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን÷ የአፍሪካ ሻምፒንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት የቅዱስ ጊዮርጊስን ሁለት ጨዋታዎች ውጤት ይጠብቃል፡፡

የአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ቡድን ባሕዳር ከተማ በውድድር ዓመት ምርጥ ውድድር ያሳለፈ ሲሆን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ክለቦች ዋንጫ ተሳትፎን ማረጋገጥ ችሏል፡፡

የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ 4 ጨዋታዎች እየቀሩት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ መሆኑን ማረጋገጡ ይታወቃል፡፡

የሊጉ ሻምፒየን መሆን ከቻለ በአፍሪካ ሻምፒንስ ሊግ የሚሳተፍ ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.