Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና ለገጣፎ ለገዳዲ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ29ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ኢትዮጵያ ቡና እና ለገጣፎ ለገዳዲ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው ለገጣፎ ለገዳዲ ከጥሩ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ጋር ሲዳማ ቡናን 3 ለ 2 መርታት ችሏል።

ካርሎስ ዳምጠው፣አማኑኤል አረቦ እና ሱለይማን ትራኦሬ የለገጣፎ ጎሎችን ሲያስቆጥሩ ያኩቡ ሞሀመድ እና መሃሪ መና ደግሞ  የሲዳማ ቡናን ሁለት ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተከናወነ ሌላ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡና መቻልን 2 ለ 1 በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማሳካት ችሏል፡፡

ጫላ ተሺታ እና ብሩክ በየነ የኢትዮጵያ ቡናን ሁለት ጎሎች ሲያስቆጥሩ ብቸኛዋን የመቻል ጎል ሳሙኤል ሳሊሶ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 42 በማድረስ ለጊዜው 4ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

 

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.