Fana: At a Speed of Life!

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ  የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀደሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባት በይፋ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ በመሆን ተሹሟል፡፡

ክለቡ ከተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በኋላ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ እና ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ድርድር መጀመራቸው ሲዘገብ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

ፋሲል ከነማ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫም ክለቡ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩትን ውበቱ አባተን በሶስት ዓመት ኮንትራት የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመከላክታል፡፡

በውድድር ዓመቱ ደካማ አቋም ያሳየው ፋሲል ከነማ በተጠናቀቀው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ በ43 ነጥብ 6ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.