Fana: At a Speed of Life!

ተደጋጋሚ ጉዳቶችና የሜዳ ላይ አቋም መቀነስ እግር ኳስ እንዳቆም አስገድደውኛል  – ሳላዲን ሰይድ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተደጋጋሚ ጉዳቶችና የሜዳ ላይ አቋም መቀነስ እግር ኳስ እንዳቆም አስገድደውኛል ሲል አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰይድ ተናገረ፡፡

ሳላዲን እግር ኳስ የማቆሙ ዜና ከተሰማ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

እግርኳስ ያቆመበትን ምክንያት ያስረዳው ሳላዲን÷ ከጉዳት ጋር በሚያጋጥመው የጤና እክሎች እና በቆይታው ምክንያት ባሳየው ደካማ አቋም ምክንያት እግር ኳስ ለማቆም መወሰኑን አብራርቷል፡፡

በቀጣይ እረፍት ለማድረግና ከቤተሰቦቹ ጋር ለማሳለፍ እቅድ መያዙን፣ ከእረፍት መልስ ደግሞ በእግርኳስ ውስጥ ባሉ ዘርፎች ሊሰማራ እንደሚችል ጠቁሟል፡፡

ከሀገር ውጭ በተለያዩ ሀገራት ሊጎች የመጫውት ዕድል የነበረው ሳላዲን÷ በተጫዋች ደረጃ ከኛ ሀገር ጋር ሲነፃፀር ምንም ልዩነት የለም ብሏል።

ልዩነቱ በሌሎች ሀገራት ትኩረት የተሰጠው የእግር ኳስ ዘርፍ በኛ ሀገር ትኩረት አለማግኘቱ ብቻ ነው በማለት ገልጿል።

ሳላዲን በአጥቂ ደረጃ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አጥቂ ዮርዳኖስ አባይ እንዲሁም ከመሃል ክፍል ደግሞ የአሸናፊ ግርማ እና ሙሉዓለም ረጋሳ አድናቂ መሆኑን ተናግሯል፡፡

በመጨረሻም በስኬታማ የእግር ኳስ ህይወቱ አስተዋፅዖ ላደረጉለት አሰልጣኞች፣ የብሄራዊ ቡድን እና የክለብ አጋሮቹ እንዲሁም  ለመላው የእግርኳስ ቤተሰብ እና ደጋፊዎች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.