Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ከ20 አመት በታች የ100 ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን ተሰበረ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ከ20 አመት በታች የ100 ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን ተሰበረ።

 

ክብረ ወሰኑን በደቡብ አሜሪካ ከ20 አመት በታች የአትሌቲካስ ሻምፒዮና ላይ፥ የሱሪናሙ አትሌት ኢሳማዴ አሲንጋ 9 ሰከንድ ከ89 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሻሽሎታል።

 

የብራዚሉ ኤሪክ ካርዶሶ እና የኮሎምቢያው ሮናል ሞስኩዬራ ውድድሩን ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

 

ክብረ ወሰኑ ከዚህ ቀደም በቦትስዋናው አትሌት ሌሲል ቴቦጎ 9 ሰከንድ ከ91 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ የተያዘ እንደነበር የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.