Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስና ባሕር ዳር ከተማ ነገ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክሉት ቅዱስ ጊዮርጊስና ባሕር ዳር ከተማ ነገ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ።

ከዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም ጋር የተደለደሉት ፈረሰኞቹ ÷ ነገ ቢሾፍቱ በሚገኘው ክብር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ዝግጅታቸውን በይፋ እንደሚጀምሩ ታውቋል።

ፈረሰኞቹ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ነሐሴ 12 ወይም 13/2015 ዓ.ም እንዲሁም የመልስ ጨዋታውን ነሐሴ 19 ወይም 20/2015 ዓ.ም እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከታንዛኒያው አዛም ጋር የሚጫወተው ባሕር ዳር ከተማም ነገ በባሕር ዳር አፄ ቴዎድሮስ ስታዲየም ዝግጅቱን እንደሚጀምር ተመላክቷል፡፡

የጣና ሞገዶቹ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ነሐሴ 12 ወይም 13/2015 ዓ.ም እንዲሁም የመልስ ጨዋታቸውን ነሐሴ 19 ወይም 20/2015 ዓ.ም ያደርጋሉ፡፡

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.