Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሴካፋ ከ18 ዓመት የሴቶች እግር ኳስ ውድድር በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈች

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበራት(ሴካፋ) ከ18 ዓመት በታች የሴቶች የእግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዛንዚባር አቻውን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።

በቻማዚ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የአጥቂ መስመር ተሰላፊዋ እሙሽ ዳንኤል በ45ኛ፣ በ55ኛ እና በ56ኛ ደቂቃ ላይ ሶስት ግቦችን አስቆጥራ ሃትሪክ ሰርታለች።

ማህሌት ምትኩ ደግሞ በ6ኛ እና በ23ኛ ደቂቃ ላይ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር፤ ትንቢት ሳሙኤል ደግሞ በ44ኛ ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥራለች።

ለዛንዚባር ብቸኛዋን ጎል ሀዋ ጁማ በ22ኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጠሯን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.