Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ወደ አሜሪካ ያቀናው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን 4 ለ 2 አሸንፏል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ በዛሬው እለት ከሎደን ዩናይትድ ጋር ጨዋታውን አድርጎ ነው 4 ለ 2 ያሸነፈው፡፡

ጎሎችን ሱራፌል ዳኛቸው፣ሽመልስ በቀለ፣አስቻለው ታመነ እና ይሁን እንዳሻው ማስቆጠራቸውን ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ቀደም ሲል የጋያና አቻውን  2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.