Fana: At a Speed of Life!

ዌስትሃም ሃሪ ማጓየር እና ዋርድ ፕራውስን ለማስፈረም ከስምምነት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዌስትሃም ዩናይትድ የማንቼስተር ዩናይትዱን ተከላካይ ሀሪ ማጓየር እና የሳውዝሃምተኑን የመሃል ክፍል ተጫዋች ጄምስ ዋርድ ፕራውስን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

ዌስትሃም ለሀሪ ማጓየር ያቀረበው 30 ሚሊየን ፓውንድ በማንቼስተር ዩናይትድ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን፥ ማጓየር ማንቼስተር ዩናይትድን የሚለቅበት ሁኔታ በተመለከተ ተጨማሪ ስምምነቶች ይደረጋሉ ተብሏል፡፡

ዌስትሃም ዩናይትደ ቀደም ሲል ለተጫዋቹ 20 ሚሊየን ፓውንድ አቅርቦ  በማንቼስተር ዩናይትድ ውድቅ እንደተደረገበት የሚታወስ ነው፡፡

እንግሊዛዊው ተከላካይ በ2019 በተካላካዮች ዝውውር ታሪክ ክብረ ወሰን 80 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ገንዘብ፥ ቀያይ ሰይጣኖችን ቢቀላቀልም በክለቡ የአራት ዓመታት ቆይታው የሚጠበቅበትን ግልጋሎት አልሰጠም፡፡

በተያያዘም ዌስትሃም ዩናይትድ የሳውዝሃምፕተኑን የመሃል ክፍል ተጫዋች ጄምስ ዋርድ ፕራውስን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሱን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

ዌስትሃም ለተጫዋቹ ቀደም ሲል 30 ሚሊየን ፓውንድ አቅርቦ ውድቅ የተደረገበት ሲሆን አሁን በተደረሰው ስምምነት የተሻለ ክፍያ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡

በዛሬው እለት ሁለት ተጫዎቾችን ለማስፈረም ስምምነት ላይ የደረሰው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ወሳኙ የመሀል ክፍል ተጫዋቻቸውን ሉካስ ፓኩዌታን ለመግዛት ማንቼስተር ሲቲ ጥያቄ አቅርቧል።

ክለቡ ለብራዚላዊው አማካይ 70 ሚሊየን ፓውንድ ቢያቀርብም መዶሻዎቹ ግን ፓኩዌታ የሚሸጥ ተጫዋች አይደለም በሚል ጥያቄውን ውድቅ አድርገውበታል።

በዚህ የዝውውር መስኮት የክለቡን ቁልፍ ተጫዋቾች ያጣው ክለቡ ለአማካዩ የተሻለ የዝውውር ገንዘብ ይዞ ሊመጣ ይችላል እየተባለ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.