Fana: At a Speed of Life!

አል ሂላል ኔይማርን ለማስፈረም ከፔ ኤስ ጂ ጋር መስማማቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲው ክለብ አል ሂላል ኔይማር ጁኒየርን ለማስፈረም ከፈረንሳዩ ክለብ ፓሪሴንት ዥርመን ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

የሁለቱ ክለብ አመራሮች በተጫዋቹ ዝውውር በመርህ ደረጃ ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን ፒ ኤስ ጂ ከብራዚላዊው ኮከብ ዝውውር 86 ሚሊየን ፓውንድ ያገኛል ተብሏል፡፡

በስምምነቱ መሰረት ኔይማር እስከ ፈረንጆቹ 2025 የሚያቆየውን ስምምነት የሚፈርም ሲሆን በቆይታውም በዓመት 129 ሚሊየን ፓውንድ ይከፈለዋል ተብሏል፡፡

የኔይማር ዝውውር በሚቀጥሉት 48 ሰዓታት የሚጠናቀቅ ሲሆን በዛሬው እለት የህክምና ምርመራውን እንደሚያጠናቅቅ ይጠበቃል፡፡

በሌላ የዝውውር ዜና የቼልሲው ግብ ጠባቂ ኬፓ አርዚባላጋ በረጅም የውሰጥ ውል ሪያል ማድሪድን ተቀላቅሏል፡፡

ኬፓ ማድሪድን የተቀላቀለቅ የክለቡ ቋሚ ግብ ጠባቂ ቲቦ ኮርቱዋ በጉዳት ምክንያት እስከ ውድድር አመቱ ከጨዋታ እንደሚርቅ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.