Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የሀንጋሪ የስፖርት ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሃንጋሪ የስፖርት ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ጋር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

በ54ኛው የዓለም አትሌቲክስ ኮንግረስ ላይ ለመሳተፍ በፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የተመራ ልዑክ ቡዳፔስት ይገኛል።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና የሃንጋሪ ስፖርት ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ታመስ ስትርበንዝ(ፕ/ር) ፈርመውታል፡፡

ስምምነቱ ከአጫጭር እስከ ድህረ ምረቃ በአትሌቲክስ ስፖርት ልማትና አስተዳደር ዙሪያ ስልጠናና መደበኛ የትምህርት እድል ለፌዴሬሽኑ ሊያስገኙ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው መባሉን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ኢትዮጵያ በረጅም ርቀት ሩጫ ያላትን ልምድ የሚያገኝበት አጋጣሚ እንደሚመቻች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.