Fana: At a Speed of Life!

ሰባስቲያን ኮን የዓለም አትሌቲክስ ኮንግረስን በድጋሚ እንዲመሩ ተመረጡ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እንግሊዛዊውን የሎሳንጀለስና ሞስኮ ኦሊምፒክ አሸናፊ ሎርድ ሰባስቲያን ኮን የዓለም አትሌቲክስ ኮንግረስን በድጋሚ እንዲመሩ ተመረጡ፡፡

በምስራቅ አውሮፖዋ ሃንጋሪ ቡዳፔስት ከተማ በቀጣይ ቀናት ከሚጀመረው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አስቀድሞ 54ኛው የዓለም አትሌቲክስ ኮንግረስ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባኤው ለቀጣይ አራት ዓመት የዓለም አትሌቲክስን በድጋሚ እንዲመሩ እንግሊዛዊው የሎሳንጀለስና ሞስኮ ኦሊምፒክ አሸናፊ ሎርድ ሰባስቲያን ኮን ድምፅ ከሰጡ 195 አባል ሃገራት የ193ቱን ይሁንታ በማግኘት መመረጣቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት ገዛኸኝ አበራና የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ዮሐንስ እንግዳ ኢትዮጵያን ወክለው በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.