Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ የወርቅ፣ ብርና ነሐስ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡዳፔስት የአለም  የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት የወርቅ፣ የብርና የነሃስ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው አስገኙ።

በሀንጋሪ እየተካሄደ ባለው  የ19ኛው የአለም  የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በመጀመሪያው ቀን የ10 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ውድድር ተካሂዷል።

በውድድሩም ጉዳፍ ፀጋይ 1ኛ፣ ለተሰንበት ግደይ 2ኛ እና እጅጋየሁ ታዬ 3ኛ በመውጣት ለሀገራቸው የወርቅ፣ የብር እና የነሃስ ለሜዳሊያዎችን አስገኝተዋል።

ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ሲፋን ሀሰን በሩጫው ማጠናቀቂያ ላይ ብርቱ ተፎካካሪ የነበረች ቢሆንም በመውደቋ አሳዛኟ ተሸናፊ ሆናለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.