Fana: At a Speed of Life!

ባሕርዳር ከተማ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከአዛም ጋር ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በካፍ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ባሕርዳር ከተማ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ከታንዛንያው አዛም ክለብ ጋር ያካሂዳል።

ጨዋታው ከቀኑ 10 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይከናወናል።

በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚሰለጥነው ባሕርዳር ከተማ÷ ለጨዋታው በባሕርዳር እና አዲስ አበባ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል።

በሴኔጋላዊው የ43 ዓመት አሰልጣኝ የሱፍ ዳቦ የሚመራው አዛም ክለብም÷ በታንዛኒያ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቶ ከትናንት በስቲያ አዲስ አበባ መግባቱ ይታወሳል፡፡

ሶማሊያዊው ሀሰን መሐመድ ሀጂ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት አንደሚመሩ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ክለቦቹ የመልስ ጨዋታቸውን ነሐሴ 21 ቀን 2015 በታንዛኒያ እንደሚያደርጉም መርሐ ግብሩ ያሳያል፡፡

በደርሶ መልስ ያሸነፈው ክለብ በቀጣዩ ዙር ከቱኒዚያው ክለብ አፍሪካ ጋር የሚጫወት ይሆናል፡፡

ባሕርዳር ከተማ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳተፈው÷ በ2015 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ተከትሎ ነው።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.