Fana: At a Speed of Life!

ስፔን የ2023 የሴቶች የዓለም ዋንጫን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2023 የሴቶች የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ስፔን እንግሊዝን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን አንስታለች።
የቡድኑ አምበል ኦልጋ ካርሞና በ29ኛው ደቂቃ ለስፔን የማሸነፊያዋን ጎል አስቆጥራለች።
የእንግሊዟ ግብ ጠባቂ ሜሪ ኢርፕስ በሁለተኛው አጋማሽ የጄኒፈር ሄርሞሶን ፍፁም ቅጣት ምት አድናለች።
የስፔኗ አይታና ቦንማቲ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ስትመረጥ፥ የእንግሊዟ ግብ ጠባቂ ሜሪ ኢርፕስ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሽልማትን አሸንፋለች።

ስፔናዊቷ ሳልማ ፓራሉሎ ደግሞ የውድድሩ ወጣት ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተመርጣለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.